የዘንድሮው ፈስቲቫል ተጋባዥ የክብር እንግዳ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ሆነ ብዙ ክለቦችን በተጨዋችነትም ሆነ በአሰልጣኝነት ያገለገሉ ክቡር አሰልጣኝ ስዩም አባተ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ታዋቂው የእግርኳስ ተጫዋች አዳነ ግርማ እና የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ዳንኤል አስገዶም ዛሬ ፍራንክፈርት በሰላም ገብተዋል:: አዳነ ግርማ በፍራንክፈርት በሚዘጋጀው ፌስቲቫል ኢትዮ አዲስን ወክሎ ይጫወታል::